ከእነዚህ ደረጃዎች መካከል ከ3መቶ90 የሚበልጡት አስገዳጅ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታውቋል።
የኢንስቲትዩቱ የህዝብ ግንኙነት ስራ አስፈጻሚ አቶ ብሩክ ሃብቴ፣ በኢትዮጵያ ከ12ሺ በላይ ምርቶች ደረጃ እንደወጣላቸው የነገሩን ሲሆን፣ ከ3መቶ90 በላይ የሚሆኑት ደረጃዎች አስገዳጅ ናቸው ብለዋል፡፡
አስገዳጅ ሲባል ከመመረታቸው በፊት ምን ማድረግ እንዳለባቸው፣ መስፈርቱን አሟልተው በተስማሚነትና ምዘና ላቦራቶሪ ተፈትሸው ማረጋገጫ ተሰጥቷቸው በዚያ መሰረት የደረጃ ምልክት / Standards Mark ኖሯቸው ገበያ ላይ የሚወጡ ናቸው በማለትም አብራርተዋል፡፡
ለቅዳሜና እሁድ ገበያዎች ጭምር ደረጃ አውጥተናል ያሉት አቶ ብሩክ፣ ደረጃው የወጣው የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴርን ጨምሮ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተሳትፈውበት ነው ሲሉም ገልጸዋል፡፡
ነገር ግን የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት ቁጥጥር እንደማያደርግ ነው የገለፁት፡፡
ቁጥጥሩን በተመለከተ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር፣ የምግብና መድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣንን ጨምሮ ሌሎችም በአዋጅ የተቋቋሙ ከ20 በላይ የመንግስት ተቆጣጣሪ አካላት እየሰሩበት ነው ብለዋል፡፡
በተያያዘም የደረጃዎች ቦርድ የገቢ ምርት የደረጃ ምልክት/ Import Standards Mark ማፅደቁ ፍትሀዊ የንግድ ውድድርን የሚያሰፍንና የሸማቾችን ደህንነት የሚያስጠብቅ እንደሆነ ተገልጿል።
የደረጃዎች ቦርድ ባሳለፈነው መጋቢት መጨረሻ ባደረገው ስብሰባ ከኢንስቲትዩቱ የቀረበውን የገቢ ምርት የደረጃ ምልክት መርምሮ አጽድቆ ነበር፡፡
አዲስአለም አበበ
ሚያዚያ 3 ቀን 2017 ዓ.ም
