በኦሮሚያ ክልል ዘመናዊ የማር አመራረት ሂደት ተግባራዊ እየተደረገ ቢሆንም፤ ወጥ የሆነ የንግድ ስርዓት ባለመኖሩ ተገቢው ጥቅም እየተገኘ እንዳልሆን
በኦሮሚያ ክልል የማር ኢኒሼቲቭ አስተባባሪ አቶ ቶሌራ ኩምሳ ከኢትዮ ኤፍኤም ጋር በነበራቸዉ ቆይታ ገልፀዋል።
አቶ ቶሌራ እንዳሉት ማር በበቂ ሁኔታ የሚመረት ቢሆንም ለ አለም ገበያ ሊቀርብ በሚችልበት ሁኔታ ላይ ግን ስራዎች አልተሰሩም ነበር ብለዋል።
አሁን ላይ ገበሬዎች ጥራቱን የጠበቀ ማር በማምረት ለዓለም ገበያ በማቅረብ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ገበሬዎቹን በማደራጀት የድጋፍና የግንዛቤ ስራ እየተሰራ እንደሆነ ሃላፊው ገልፀዋል ።
1.5 ሚሊዮን ዘመናዊ የማር እርባታ ቀፎ ለገበሬዎች ማቅረባቸውንም አቶ ቶሌራ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡
በዘንድሮ ዓመት ብቻ 37 ሜትሪክ ቶን ማር ለዓለም ገበያ እንደቀረበ የተገለፀ ሲሆን በአማካይ አንድ ኪሎ ግራም ማር በስድስት ዶላር መሸጡ ተነግሩዋል።
ልዑል ወልዴ
ሚያዚያ 06 ቀን 2017 ዓ.ም
