በዓሉ በነገው ዕለት በወዳጅነት አደባባይ እንደሚከበር የአዲስ አበባ የሲዳማ ኮሚኒቲ ማህበር አስታውቋል።
በዓሉ በዓለም የማይዳሰሱ ቅርስነት ከተመዘገበ ዘንድሮ 10ኛ አመት ክብረበዓሉ ላይ ይገኛል።
የማህበሩ የቦርድ ሰብሳቢ ዶክተር አስቻለው አባይነህ፤ባለፉት 5 ዓመታት በአዲስአበባ ሲከበር መቆየቱን አንስተው፤በዚህኛው ዓመት በዩኔስኮ የተመዘገበበት አስረኛ አመቱንም ምክንያት በማድረግ ይከበራል ብለዋል።
የሲዳማ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ የሆነው “ፊቼ ጫምባላላ” በሀዋሳ ጉዱማሌ መጋቢት 19 መከበሩ ይታወሳል።
የሲዳማ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ “ፍቼ ጨምባላላ” ከአስር ዓመታት በፊት በተባበሩት መንግሥታት የሳይንስ እና ባህል ድርጅት “ዩኔስኮ” የሰው ልጆች ወካይ የዓለም ቅርስ ሆኖ መመዝገቡ የሚታወስ ነው።
በዓሉ ጫምባላላ ከተከበረበት የመጀመሪያው ቀን አንስቶ ለተከታታይ 15 ቀናት የሚከበር ነው።
እስከዳር ግርማ
ሚያዚያ 3 ቀን 2017 ዓ.ም
