ተመድ እንዳለዉ በጋዛ የሚገኙ ከ70 በመቶ በላይ የሚሆኑ ትምህርት ቤቶች በቀጥታ በእስራኤል ጥቃት የደረሰባቸዉ ናቸዉ፡፡
በጋዛ የሚገኙ 88 በመቶ የሚሆኑ ትምህርት ቤቶች ዕድሳት እና ከፍተኛ ጥገና የሚስፈልጋቸዉ ናቸዉ ሲል ድርጅቱ አስታዉቋል፡፡
በተባበሩት መንግስታት የተሰሩ 1መቶ 62 ትምህርት ቤቶችም ዕድሳቱ የሚያስፈልጋቸዉ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ድርጅቱ የእስራኤል ጥቃት የጋዛ ልጆችን ያፈናቀለ፣ ያስጨነቀ እና የመማር መብታቸዉን የነፈገ ነዉ ብሏል፡፡
ትምህርት በጋዛ የጦር ጉዳተኛ ሆኗል ሲል ድርጅቱ ገልጿል፡፡
ጥቅምት 7 በጋዛ ጦርነቱ ከተጀመረ ጀምሮ ሴቶች እና ህጻናትን ጨምሮ ከ51 ሺህ በላይ ፍልስጤማዊያን ህይወታቸዉ አልፏል ሲል አናዶሉ ዘግቧል፡፡
እስከዳር ግርማ
ሚያዚያ 7 ቀን 2017 ዓ.ም
