የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት እንደ ገለጸዉ በየትኛዉም መልኩ በህገወጥ እርድ ሚቀርብ ስጋ ህብረተሰቡን ለበርካታ በሽታዎች ሊያጋልጥ እንደሚችል ገልጿል፡፡
የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ አታክልቲ ገብረ ሚካኤል፤በዘርፉ ላይ የተደረጉ ጥናት እንደሚያስረዱት ከእንስሳት ወደ ሰዉ የሚተላለፉ 2 መቶ የሚደርሱ በሺታዎች መኖራቸዉን ገልጿል፡፡
አቶ አታክልቲ ፈጣን የህይወት ህልፈት የሚያስከትለዉን አባ ሰንጋን ጨምሮ የእድሜ ልክ መሃንነት የሚያስከትሉ የዉርጃ በሺታዎች እንዲሁም የሳንባ ነቀርሳ በሽታዎች ከእንስሳት ወደ ሰዉ ይተላለፋሉ ካሏቸዉ መካከል ናቸዉ፡፡
ህብረተሰቡ እነዚህን በሽታዎች ለመከላከል ጤናዉ የተጠበቀን ስጋን ከትክክለኛ ቦታ በመግዛት እንዲተቀም የቄራዎች ድርጅት መክሯል፡፡
መጪዉን የፋሲካ በዓል አስመልክቶ 4ሺህ የሚደርሱ ትላልቅ እንስሳት እና ከ2ሺህ 5 መቶ በላይ በግና ፍየል ይገባል ተብሎ ይጠበቃል ሲል የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ጠቁመዋል፡
ልኡል ወልዴ
ሚያዚያ 7 ቀን 2017 ዓ.ም
