በመዲናችን ከ3መቶ ሺህ በላይ ለሚሆኑ ነዋሪዎች የነዋሪነት መታወቂያ መሰጠቱ ተገለጸ፡፡

በዕቅድ ተይዞ ከነበረዉ 4መቶ73 ሺህ በላይ የነበር ሲሆን፤ 3መቶ39ሺህ በላይ ለሚሆኑ ነዋሪዎች መታወቂያ ሰጥቻለሁ ሲል የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ አስታዉቋል፡፡

አገልግሎቱ እነዚህ መታወቂያዎች በአዲስ፣ በእድሳት፣ በእርማት እና በምትክ የተሰጡ መሆናቸዉን አንስቷል፡፡

ከዚህ ቁጥር ዉስጥ 97 በመቶዎቹ ዲጅታል መታወቂያ የተሰጣቸዉ ሲሆን፤ ቀሪዉ ለአቅመ ደካሞች እና ለአካል ጉዳተኞች የተሰጠ ነዉ ብሏል፡፡

በከተማዋ ከ64ሺህ በላይ ህጻናትን በተወለዱ በ90 ቀናቸዉ የልደት ምዝገባ ማድረጉን ያስተወቀዉ አገልግሎቱ፤ ካለፈዉ ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ71 በመቶ ብልጫ አለዉ ብሏል፡፡

የልደት፣ጉዲፈቻ፣ ጋብቻ፣ ፍቺ እና ሞት ምዝገባ ከ3መቶ8ሺህ በላይ ለመመዝገብ ታቅዶ እንደነበርም ተነስቷል፡፡

በዚህም አጠቃላይ ምዝገባዉ ካለፈዉ ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ1.52 በመቶ ቅናሽ አሳይቷል ተብሏል፡፡

ቅናሽ ካሳዩ ምዝገባዎች መካከል ጋብቻ አንዱ ሲሆን፤ ፍቺ በንፅፅር ብልጫ አሳይቷል።

በአሁኑ ወቅት ጤና ተቋማት ፣ የጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት እና የፌደራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤቶች በድምሩ 1መቶ70 ማዕከላት ከመደበኛ ቢሮ ውጭ የወሳኝ ኩነት የአንድ ማዕከል ምዝገባ አገልግሎት የሚሰጥባቸው ማዕከላት መሆናቸዉ ተገልጿል፡፡

ሰንፔር እንዳለዉ

ሚያዚያ 7 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *