በቀን ከ3ሺህ 5 መቶ በላይ እርድ እየከወንኩ  ነዉ ሲል የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት አስታወቀ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ቄራዎች ድርጅት እንደገለፀው አሁን ላይ  በቀን ከ3ሺህ 5 መቶ በላይ ከትላልቅ እስከ ትናንሽ እንስሳት እርድ እየከወነ እንዳለ  ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታዉቋል፡፡

የድርጅቱ የህዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊ አቶ አታክልቲ ገብረ ሚካኤል፤ድርጅቱ ከ1949 ዓ.ም ጀምሮ ለ66 ዓመት ንጽህናዉን የጠበቀ የእርድ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ገልፀው  ተቋሙ ከዚህ በፊት በቀን ከ3መቶ ያነሰ እርድ ይከውን  ነበር ያሉ ሲሆን  አሁን ላይ በቀን ከ3ሺህ 5መቶ በላይ ማድረሱን ገልጸዋል፡፡

ይህ ቁጥር የበዓላት ወቅትን አያካትትም ያሉት አቶ ኣታክልቲ ፤በበዓላት ወቅት ቁጥሩ ከዚህም በላይ እንደሆነ አንስተዋል።

የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት በየመንገዱ በስርጭት ወቅት የሚገጥሙ ችግሮችን ለመለየት፤ለየትኛዉ ድርጅት በየትኛዉ ሠዓት አስረከበ የሚለዉን ዘመናዊ የጂፒየስ ቴክኖሎጂ በአሽከርካሪዎች ላይ በመግጠም የሚከሰት መስተጓጉልን እንዳሶገደም  አብራርተዋል፡፡

ከ60 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገዛ የተረፈ ስጋ ማቀነባበሪያ ማሽን መትከሉን ቄራዎች ድርጅት ጠቁመዋል።

ልዑል ወልዴ

ሚያዚያ 8 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *