ከአስር ሺህ በላይ ለሚሆኑ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ አረጋውያን እና ሌሎች ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች ከ63 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ድጋፉ መደረጉ ተገልጿል።
ባንኩ አዲስ አበባን ጨምሮ በመላው ሃገራችን ከአንድ መቶ በላይ በሚሆኑ የድጋፍ መስጫ ጣቢያዎች ድጋፍ ማድረጉን አስታውቋል።
አዋሽ ባንክ ህዝባዊ እና ሃይማኖታዊ በዓላትን ምክንያት በማድረግ በዝቅተኛ ገቢ ለሚተዳደሩ አቅመ ደካሞች ድጋፎችን እያደረገ እንደሆነም ተገልጿል፡፡
አዋሽ ባንክ የ2017 የፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድረግ አዲስ አበባን ጨምሮ በመላው ሃገራችን ከአንድ መቶ በላይ በሚሆኑ የድጋፍ መስጫ ጣቢያዎች ከአስር ሺህ በላይ ለሚሆኑ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ፣ጧሪ ለሌላቸው አረጋውያን እና ሌሎች ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች ከ63 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ለበዓሉ የዓይነትና የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉን ገልጿል።
አዋሽ ባንክ የህብረተሰቡን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ላለፉት 30 ዓመታት በርካታ ማህበረሰብ ተኮር ስራዎችን በመስራት በተለያዩ ጊዜያት በሰው ሰራሽ እና በተፈጥሮ አደጋ ለተጎዱ የማህበረሰብ ክፍሎች ዘርፈ ብዙ ድጋፍ ሲያደርግ ቆይቷል፤እያደረገም ይገኛል፡፡
አፎሚያ አሸናፊ
ሚያዚያ 8 ቀን 2017 ዓ.ም
