መጪውን የፋሲካ በአል አስመልክቶ የኮሚሽኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ በሰጡት መግለጫ ወደ ከተማዋ የሚገቡ ለበዓሉ የሚያስፈልጉ ግብአቶችን ለይቶ ማስገባቱን ተናግረዋል።
ኮሚሽኑ በመዲናዋ በሚገኙ 239 ሉካንዳ ቤቶች የነዋሪውን ፍላጎት መሰረት ባደረገ መልኩ አንድ ኪሎ ስጋን ከ460 ብር ጀምሮ እስከ 520 ብር ማቅረብ መጀመሩንም አስታውቋል።
ኮሚሽኑ ወደ 154 የሚጠጉ ማህበራት በስሩ ያሉ ሲሆን ለበዓል ሙሉ ዝግጅት እንዳደረጉ እና ስራዎች መሰራታቸው ተነስቷል።
ወ/ሮ ልዕልቲ በተጨማሪም የኢንዱስትሪ ምርቶች የሆኑትን እንደ ዘይት ዱቄት እና መሰል ግብአቶች በባዛር ለአንድ ሳምንት የሚቆይም አድርገናል ብለዋል።
ከዚህ ባለፈም በመቸርቸሪያ ቦታዎችም በቂ ዝግጅት አድርገናል ሲል ኮሚሽኑ ገልጿል።
ወ/ሮ ልዕልት የስጋ ዋጋው አነሰ ማለት ስጋው ጥራት የለውም ሳይሆን ልኳንዳ ቤቶቹ የኪራይ ቤት ስልላሆነ ጫና ስለሌለባቸው ነው የተቀነሰው ብለዋል።
ልኳንዳ ቤቶቹ በአል ሲመጣ ኪራይ ነፃ ይደረግላቸዋል ያሉ ሲሆን ይህ የስጋ ዋጋም በዚሁ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል።
ለዓለም አሰፋ
ሚያዚያ 9 ቀን 2017 ዓ.ም
