ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ359 ሺህ በላይ ዜጎችን በውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ተጠቃሚ አድርጊያለሁ አለ የስራና ክህሎት ሚኒስቴር

የስራና ክህሎት ሚኒስቴር በበጀት ዓመቱ ከእስከ መጋቢት 30 ድረስ፣ 359 ሺህ 291 ዜጎችን በውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል ሲል አስታውቋል፡፡

ሚኒስቴሩ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ዕቅድ አፈፃፀሙን አምባሳደር ግርማ ብሩ በተገኙበት መገምገሙንም ይፋ አደድርጓል፡፡ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በተካሄደው በዚህ መድረክ ከሰለጠነ የሰው ሃይል አቅርቦት፣ ከሥራ ገበያው ፍላጎት እና ከአገልግሎት አሰጣጥ አኳያ የተከናውኑ ሥራዎች ላይ ውይይት መደረጉን የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ገልጿል፡፡

ካለው የሥራ ገበያ ፍላጎት አኳያ አቅርቦት እና ጥራት ላይ ያሉ ችግሮችን በመፍታት ውጤቱን ለማላቅ እና የዜጎችን ተጠቃሚነትን ለማሳደግ ርብርብ ማድረግ እንደሚገባም መግባባት ላይ ተደርሷል ብሏል፡፡

በዘርፉ በመንግስትና በግል ተቋማት የሚሰጠው ሥልጠና የሥራ ገበያውን ፍላጎት የሚመልስ እና ፍላጎትና አቅርቦቱን ማጣጣም የሚያስችል መሆኑን የማረጋገጥ፣ እንዲሁም ማነቆዎችን መፍታትና ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫችን ዋነኛ ማጠንጠኛ ሆኗል ነው የሚለው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ፡፡

እንደ የስራና ክህሎት ሚኒስቴር አገላለጽ “በዘርፉ የተጀመረው የዜጎችን መብት፣ ደህንነትና ተጠቃሚነት የማረጋገጥ ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል”

ህገ-ወጥነትን መከላከልና ህግና ስርዓትን ማስከበርም በልዩ ሁኔታ ተጠናክሮ ይቀጥላል ያለው ሚኒስቴሩ፣ ለዚህም በየደረጃው የሚመለከታቸው ባለድርሻና አስፈፃሚ አካላት ሁሉን አቀፍ ርብርብ ማድረግ ይኖርባቸዋል በማለት አሳስቧል፡፡

ሚያዚያ 15 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *