የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ሞስኮ አፍሪካ በአዲሱ ዓለም አቀፍ ሥርዓት ውስጥ ነጻ ተዋናይ እንድትሆን ለመርዳት ቁርጠኛ ነች ብለዋል።
ላቭሮቭ ሩሲያ ለአፍሪካ ልማት ያላት ቁርጠኝነት በሉዓላዊነት፣በትምህርት፣በላቁ ቴክኖሎጂዎች ተደራሽነት ላይ ያተኮረ እንደሆነ ጠቁመዋል።
ሩሲያ ለአፍሪካ የነጻነት ንቅናቄዎች ያደረገችውን ድጋፍ በማስታወስ ከአህጉሪቱ ጋር ያላትን ታሪካዊ የወዳጅነት ትስስር አጉልተዋል።
ላቭሮቭ አክለውም ሩሲያ እና የአፍሪካ አጋሮቿ አዲስ ቅኝ አገዛዝን ለመቃወም እና ገለልተኛ የኢኮኖሚ መፍትሄዎችን ለመመስረት በጋራ እየሠሩ መሆናቸውን አንስተዋል።
በሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ትብብር ቢሮ ኃላፊ ታትያና ዶቭጋለንኮ በሩሲያ እና አፍሪካ ግኑኝነት ዙሪያ ትኩረቱን ባደረገው ፎረም ላይ ባደረጉት ንግግር ሩሲያ እና አፍሪካ ተፈጥሯዊ አጋሮች ናቸው ብለዋል።
“የአፍሪካ አጋሮቻችን ሩሲያ የአዲሱ ባለብዙ ማዕከል ዓለም አንዷ መሪ እንደሆነች እንዲሁም ሉዓላዊነቷን መከላከል የምትችል እና ሌሎች ሀገራትንም በዚህ የመርዳት አቅም እንዳላት ማወቃቸው አስፈላጊ ነው” ብለዋል።
የአህጉሪቱ ሀገራት በሩሲያ ላይ በሚጣሉ ማዕቀቦች ላይ አልተሳተፉም ሲሉም ዲፕሎማቷ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።
“አህጉሪቷ ቀስ በቀስ ራሱን የቻለች ዓለም አቀፍ ተዋናይ እየሆነች እና በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ የፖለቲካ ተጽዕኖዋ እየጨመረ መጥቷል።
ለአፍሪካ ችግሮች-የአፍሪካ መፍትሄዎች በሚለው ሀሳብ መሠረት አፍሪካ በተቋማት ላይ ትኩርት እያደረገች እና የአፍሪካ ሀገራትን ትብብር እያጠናከረች ነው” ሲሉ ዶቭጋለንኮ ተናግረዋል ሲል ስፑትኒክ ዘግቧል ።
ሚያዚያ 16 ቀን 2017 ዓ.ም
