ቅዳሜ ምሸት 5:00 ላይ ሪያል ማድሪድ ከ ባርሴሎና ( በትልቁ ደርቢ ኤልክላሲኮ) በኮፓ ዴል ሬይ የፍፃሜ ጨዋታ ይፋለማሉ።

ሪያል ማድሪድ በዚህ የውድድር ዓመት ካለው የተጨዋች ስብስብ አንፃር የውድድር ዘመኑ ከመጀመሩ አስቀድሞ ትልቅ ግምት ቢሰጠውም ወጥ ብቃት ለማሳየት ሲፈተን ቆይቷል፡፡ የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና የሶስትዮሽ ዋንጫ ለማሳካት መንገድ ላይ ይገኛል፡፡

በጀርመናዊው አሰልጣኝ ሀንሲ ዲተር ፍሊክ የሚመራው ባርሴሎና በኮፓ ዴል ሬይ የፍፃሚ ተፋላሚ ሲሆን፤ በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ደግሞ የግማሽ ፍፃሜ ተፋላሚ መሆኑ አይዘነጋም በተጨማሪም ላሊጋውን ከተከታዩ ሪያል ማድሪድ በአራት ነጥብ ርቆ 1ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡

የባርሳዎቹ ላሚን ያማል፣ ፌራን ቶሬስ፣ ዳኒ ኦልሞ ፣ፔድሪ፣ ጋቪ፣ ሮበርት ሎንዶውስኪ እና ራፊንህን የመሳሰሉ ከዋክብቶች በዚህ ቡድን ውስጥ ታሪክ ለመስራት የተዘጋጁ ተጨዋቾች ሆኖዋል።

በማሪንጌዎቹ በኩል ኪሊያን ምባፔ፣ ቪኒሸስ ጁኒየር፣ ቤሊንግሀም እና ሮድሪጎን የመሳሰሉ ኮከቦች ማድሪድን ለአሸናፊነት ለማበቃት ይጠበቃሉ።

በተለይ ክርቲያኖ ሮናልዶ እና ሊዮኔል ሜሲ ስፔንን ከለቀቁ በኋላ ደርቢው መቀዛቀዝ ታይቶበት የነበር ሲሆነ፡፡ አሁን ላይ በአዳዲስ ክዋክብቶች ኤልክላሲኮ ወደቀደመ ፉክክሩ እየመጣ ይመስላል፡፡

በሁሉም ውድድር ባደረጓቸው ያለፉት አምስት ጨዋታዎች ባርሴሎና ሶስቱን ሲያሸንፍ ሪያል ማድሪድ ሁለቱን አሸንፏል፡፡ሁለቱ ቡድኖች በኮፓ ዴል ሬይ የፍፃሜ ጨዋታ ነገ ምሽት 5 ሰዓት ላይ ይገናኛሉ፡፡

ጋዲስ መገርሳ

ሚያዚያ 17 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *