ግማሽ ሚሊዮን አዲስ ተፈናቃዮች በጋዛ መኖራቸው ተገለፀ።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በእስራኤል ጦር የተሰጡ በርካታ የማፈናቀል ትእዛዞች ፍልስጤማውያን በጋዛ ከአንድ ሶስተኛ ባነሰ አካባቢ እንዲኖሩ አድርጓቸዋል ብሏል።

ባለፉት ወራት በጋዛ 5መቶ ሺህ የሚጠጉ ፍልስጤማውያን በእስራኤል ጦር ጥቃት ሳቢያ በግዳጅ መፈናቀላቸውን የተባበሩት መንግስታት የፍልስጤም ስደተኞች ኤጀንሲ አስታውቋል።

ድርጅቱ በሰጠው መግለጫ ባለፈው ወር በጋዛ ወደ ግማሽ ሚሊዮን የሚጠጉ አዲስ ዜጎች ተፈናቅለዋል።

በእስራኤል ጦር በተሰጡ በርካታ የማፈናቀል ትእዛዛት ፍልስጤማውያን በጋዛ ከአንድ ሦስተኛ ያነሰ ቦታ ላይ እንዲኖሩ አድርጓቸዋል፤ የቀረው ቦታም የተበታተነ ፣ደህንነቱ ያልተጠበቀ እና ለኑሮ ምቹ ያልሆነ ነው ብሏል።

መጠለያዎች በአስከፊ ሁኔታ ውስጥ ናቸው። አገልግሎት ሰጪዎችም ለመሥራት እየታገሉ ቢሆንም ያለው ግብዓትም እየተሟጠጠ ነው ብሏል።

ከጥቅምት 2023 ጀምሮ አብዛኞቹ ሴቶች እና ህፃናት የሆኑ 51 ሺህ 4መቶ የሚጠጉ ፍልስጤማውያን በጋዛ ተገድለዋል።

ሰንፔር እንዳለው

ሚያዚያ 17 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *