ፒኤስጂ አርሰናልን በማሸነፍ በሻምፒየንስ ሊግ ለሙኒኩ ፍፃሜ ደረሰ !

በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ግማሽ ፍፃሜ የመልስ ጨዋታ ፒኤስጂ ከአርሰናል ጋር ያደረገውን ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

የፒኤስጂን የማሸነፊያ ግቦች ፋብያን ሩይስ እና አሽራፍ ሀኪሚ ሲያስቆጥሩ ቡካዩ ሳካ የአርሰናልን ግብ ከመረብ አሳርፏል።

ፒኤስጂ በድምር ውጤት አርሰናልን 3ለ1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ለሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ ማለፋቸውን አረጋግጠዋል።

በአሰልጣኝ ሉዊስ ኤንሪኬ የሚመራው ፒኤስጂ በታሪክ ለሁለተኛ ጊዜ ለሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ አልፈዋል።

ፒኤስጂ የፍፃሜ ጨዋታውን ከኢንተር ሚላን ጋር ጀርመን ሙኒክ ላይ የሚያደርጉ ይሆናል።

የዘንድሮው የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ ጨዋታ ቅዳሜ ግንቦት 23/2017 ዓ.ም ሙኒክ አሊያንዝ አሬና ስታዲየም ላይ ይደረጋል።

ጋዲሳ መገርሳ

ሚያዚያ 30 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *