በፀጥታ ችግር ምክንያት የነዳጅ አቅርቦት እጥረት መከሰቱን የአማራ ክልል ንግድ ቢሮ ገለፀ።

በክልሉ በባለፉት ሁለት ወዲህ እየተፈጠረ ያለዉ አለመረጋጋት ለእጥረቱ መከሰት እንደምክንያት ተቀምጧል።

በአማራ ክልል ንግድና ገቢያ ልማት ቢሮ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ታፈረ ይመር ለጣቢያችን እንዳሉት በባለፉት ሁለት አመታት በክልሉ ተፈጥሮ በነበረዉ ግጭት ምክንያት መንገድ ላይ ያለዉ የፀጥታ ችግር መግጠሙን ተናግረዋል።

ቦቴዎች በነፃነት ነዳጅ ጭነዉ ለመግባትና ለመዉጣት ግዴታ በመንግስት አካል ካልታጀቡ ሹፌሮች እንደሚገደሉና እንደሚታገዱ የገለፁት አቶ ታፈረ ይህም አቅርቦቱ ላይ ተፅእኖ እያሳደረ እንደሆነ ገልፅዋል።

አሁን ላይ የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም ከፌደራል ነዳጅና ንግድና ቀጣናዊ ጋር በመነጋገር ያለዉን አቅርቦት በሁሉም አካባቢዎች ለማድረስ እየተሰራ እንደሚገኝና ይህ ሲባል ግን ችግሩ ሙሉ ለሙሉ አለመቀረፉን ተናግረዋል።

ምርቶችን ቸርቻሪዎች ለህብረተሰቡ በተገቢዉ ሁኔታ ባለማድረሳቸዉና ምርቱን ከመጠቅም ይልቅ በጥቁር ገቢያ የመሸጥ ሁኔታዎች ስላሉ ክትትል በማድረግ ምርትን በመዉረስ ለመንግስት ገቢ እየሆነ እንዳለ ገልፅዋል።

ሊዲያ ደሳለኝ

ሚያዚያ 30 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *