ሩሲያ የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ሩሲያ ገብተው ላበረከቱት አገልግሎት ሽልማት መስጠቷ ተገለጸ፡፡
የሩሲያ ባለስልጣናት እንዳሉት ወታደሮቹ በኩርስክ ግዛት በነበረው ኦፕሬሽን ትልቅ ሚና ስለመጫወታቸው መግለጻቸውን የሃገሪቱ የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል፡፡
በሰሜን ኮሪያ የሩሲያው አምባሳደር አሌክሳንደር ማትሴጎራ ሩሲያና ሰሜን ኮሪያ ስልታዊ አጋርና ጥብቅ ወዳጆች መሆናቸውን ስለመግለጻቸው የሰሜን ኮሪያ ማእከላዊ የዜና ኤጀንሲ ገልጹዋል፡፡
አምባሳደሩ እንዳሉት ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ለሩሲያ ላበረከቱት ህይወትን እስከመስጠት ለደረሰው መስዋትነታቸው ወታደሮቹን የሰሜን ኮሪያ ህዝብንና እንዲሆም ፕሬዝዳንቱን ኪም ጆንግን አመሰግናለው ብለዋ ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
ባለፈው ወር መጨረሻ ሰሜን ኮሪያ ሩሲያ ከዩክሬን ጋር የምታደርገውን ጦርነት ለማገዝ ወደሩሲያ ወታደሮቹዋን መላኩዋን አረጋግጣለች ሲል የዘገበው የአናዱሉ ነው፡፡
ገነነ ብርሃኑ
ግንቦት 1 ቀን 2017 ዓ.ም
