አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ በአገሪቷ በአግባቡ በመተግበር መጠቀም እንዲቻል የመንግስትና የግሉ ዘርፍ ሚና ከፍተኛ ነውም ተብሏል።
ይህ የተገለፀው በኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ዙሪያ ከግሉ ዘርፍ ጋር አብሮ መስራት የሚችለበት የውይይት መድረክ በተካሄደበት ወቅት ነው።
በመድረኩ የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ተቋም ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ወርቁ ጋቸና ፤ኢኒስቲትዩቱ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ የሀገሪቱን ተጠቃሚነት ከማሳደግ ረገድ በርከት ያሉ ተግባራትን መከወኑን አስታውቋል።
ሰው ሰራሽ አስተውሎ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በሰዎች ህይወት ውስጥ ያላው ወሳኝ ሚና እየጨመረ መጥቷል ሲሉ ዳይሬክተሩ ገልፀዋል።
ተጽእኖው በተለያዩ ኢንዱስትሪዎች እና ዘርፎች ላይ ከጤና አጠባበቅ እስከ ፋይናንስ፣ ከትራንስፖርት እስከ ንግድ ፣ ሰው ሰራሽ አስተውሎ የምንኖርበትን እና የምንሰራበትን መንገድ እያሻሻለ ነው፣ ይህም ህይወታችንን በማናስበው መንገድ ቀላል ያደርገዋል ነው ያሉት።
ሆኖም ግን መረጃን የምሰጥበትም ሆነ የምናገኝበት የአገሪቱ የመረጃ ፖሊሲ ዘርፉ በስፋት ሊሰራበትና ሊመራመርበት የሚችልበትን አቅም ገድቦታል ብለዋል።
አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ በስራ እና በግላዊነት ላይ ስላለው ተጽዕኖ በእርግጠኝነት ስጋቶች ቢኖሩም፤ የዚህ ቴክኖሎጂ ጥቅሞችን ግን ችላ ማለት ከባድ ነው ሲሉም አስረድተዋል።
አገራት ቴክኖሎጂን በመጠቀም በተለያዩ ዘርፎች ውጤታማ እየሆኑ መሆኑን ጠቅሰው አርትሬፊሻል ኢንተለጀንስ ዋነኛ የዕድገት መሳሪያ እየሆነ መምጣቱን አንስተዋል።
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ብሩክ ታዬ ፤ዘርፉ ለአገር እድገት የሚያበረክተውን አስተዋጽኦ ለማጉላት መንግስት የተለያዩ ስትራቴጂዎችን ቀርጾ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ አዲስ ቢሆንም በፍጥነት እያደገ የመጣ ተቋም መሆኑን ጠቅሰዋል።
በዚህ ዘርፍ ሃሳብ ያላቸውን ተመራማሪዎችን ለመደገፍ ከፖሊሲ ጀምሮ የፋይናንስ ድጋፍ የሚደረግ መሆኑን ገልፀዋል።
በዘርፉ በትኩረት እየሰራበት ካሉት ሶስት መሰረታዊ ጉዳዮች መካከል የግሉን ዘርፍ የግንዛቤ ማሳደግ ፣የመሰረተ ልማትና የቴክኖሎጂ ድጋፍ፣እንዲሁም ከ60 በላይ የሆኑ የፈጠራ ሃሳብ ያላቸውን ተመራማሪዎች የማገናኘትና የማስተሳሰር ተግባር መሆኑን ሰምተናል።
ልኡል ወልዴ
ግንቦት 1 ቀን 2017 ዓ.ም
