በጋዛ ከ65ሺህ በላይ ህጻናት በከፍተኛ ረሃብ ምክንያት ለሞት የተጋለጡ ናቸዉ ተባለ፡፡

የጋዛ መንግስት በጋዛ ሰርጥ ከ65 ሺህ በላይ ህጻናትን ህይወት እያሰጋ ያለ የረሃብ አደጋ ተጋርጧል ሲል አስጠንቅቋል፡፡

ከሁለት ወራት በላይ የቀጠለዉ የእስራኤል እርዳታ እና አስፈላጊ አቅርቦቶች ላይ የተደረገ ገደብ ሁኔታዉን አባብሶታል ተብሏል፡፡

በጋዛ ሰርጥ የሚገኘው የመንግስት የሚዲያ ፅህፈት ቤት በሰጠው መግለጫ፤ የእስራኤል ወረራ በረሃብ ምክንያት ሰላማዊ ሰዎችን እየገደለ ነው ብሏል።

ማቋረጫ መንገዶችን በመዝጋት እና 39 ሺህ እርዳታ፣ ነዳጅ እና መድሀኒት የጫኑ መኪኖች እንዳይገቡ በመከልከል ከ2.4 ሚሊዮን በላይ ሰላማዊ ዜጎች ላይ ስልታዊ ወንጀሎችን እየፈፀመ ሲሆን ፤ይህም አለም አቀፍ ህግን የጣሰ ነዉ ብሏል በመግለጫዉ፡፡

መግለጫው አክሎም ፤በጋዛ ሰርጥ የሚገኙ ዳቦ ቤቶች በሙሉ ከአገልግሎት ውጪ በመሆናቸዉ፤ ለ40 ቀናት ያህል ነዋሪዎች መሠረታዊ የሆነውን ምግብ ባለማግኘታቸዉ በተለይም በሕፃናት፣ በሕሙማንና በአረጋውያን ላይ ረሃብና የምግብ እጥረት እየተባባሰ መምጣቱን አስታውቋል።

እስራኤል ረሃብን በሰላማዊ ሰዎች ላይ በመሳሪያነት በመጠቀሟ ከ65 ሺህ በላይ ህጻናት በተመጣጠነ ምግብ እጥረት እና በምግብ እጥረት ለሞት ተጋልጠዋል ብሏል።

መግለጫው እስራኤል ለ70 ቀናት የመሻገሪያ መንገዶችን ሙሉ በሙሉ በመዝጋቷ የሰብአዊ እና የጤና ሁኔታ እየተባባሰ መጥቷል ሲል አስታዉቋል፡፡

ሐመረ ፍሬዉ

ግንቦት 4 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *