የአፋር ንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት አባላቱን ማግኘት እንዳልቻለ ገለፀ።

ምክር ቤቱ በሰሜኑ ጦርነት በክልሉ የደረሰዉን ዉድመት ተከትሎ የንግዱን ማህበረሰብ ህልዉና መመለስ እንዳልተቻለ ገልጿል።

የአፋር ንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ዋና ፀሀፊ አቶ ሀሰን ኡስማን በ18 ወረዳዎች ላይ የነበሩ የንግድ ተቋማት ከፍተኛ ወድመት እንደደረሰባቸዉ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።

በጦርነቱ ምክንያት ምክር ቤቱ አባላቱ እንደተበተኑበት የሚናገሩት ዋና ፀሀፊዉ የተበተኑ አባላትን ለመሰብሰብ አለመቻሉን ገልፅዋል ።

ዋና ፀሀፊዉ አሁን ላይ ምክር ቤቱ  ባለዉ አቅም 9 ወረዳዎች ላይ ብቻ መድረስ  ነዉ የቻለዉ ብለዋል።

አባላቱን ለመሰብሰብ በክልሉ ንግድ ቢሮ የንግድ ፍቃድ እድሳት ለማድረግ የሚመጣዉን የንግዱ ማህበረሰብ ለምክርቤቱ አባልነት ምዝገባ እንዲያደርጉ እየተሞከረ ነዉ ተብሏል።

አቶ ሀሰን በተጨማሪም የምክር ቤቱ ገቢ ከአባላት የሚሰበሰብ መዋጮ የሚገኝ ነበር ያሉ ሲሆን፣ ሆኖም ያሉ አባላትም ኢኮኖሚያዊ  አቋም  ያን ለማድረግ የሚያስችል አይደለም ሲሉ ተናግረዋል።

የአፋር ንግድ  እና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ለንግዱ ማህበረሰብ የሚጠበቀበትን አላደረገም ሲሉ ነው ዋና ፀሐፊው የተናገሩት።

ከመዋቅር ማሻሻያ ጀምሮ በክልሉ የንግዱ ማህበረሰብ ካለበት አቋም አንፃር የሚጠየቀዉን መንግስታዊ መዋጮ ሚዛናዊ እንዲሆን ለማስቻል ምክር ቤቱ እየሰራሁ ነው ብሏል።

ቁምነገር አየለ

ግንቦት 4 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *