በትግራይ አስፈጻሚ አካላት ለህግ ባለመገዛታቸው የሚቀርቡ አቤቱታዎች በሚመጡት ልክ ምላሽ እያገኙ አይደለም ተባለ።

አቤቱታዎችን አንፈጽምም ያሉ 7 ተቋማትም የተገኙ ሲሆኑ ከ7ቱ አምስቱ በክስ ላይ እንዳሉም ተሰምቷል፡፡

ስራቸውን በሀላፊነት አንፈጽምም ካሉት ተቋማት መካከልም “ትግራይ ቴሌቪዥን” እንደሚገኝበት የነገሩን በሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም የትግራይ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ሀላፊው አቶ ጸሃዬ አምባዬ ናቸው፡፡

የሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም የትግራይ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት እንደገለጸው፣ በትግራይ ተጠሪ ተቋማት ያለመኖር እንዲሁም ተጠሪ በሆኑ ተቋማትም ያሉ ሃላፊዎች ውሳኔዎችን ለማስፈጸም ፍቃደኛ ባለመሆናቸው ምክንያት አቤቱታዎችን ማስተናገድ እንዳለቻሉም ነግረውናል፡፡

የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ሃለፊ አቶ ጸሃዬ እምባዬ ፤ በ9 ወራት ውስጥ 135 አቤቱታዎችን መቀበላቸውን የገለጽ ሲሆን ሁሉም በአካል የቀረቡ አቤቱታዎች ናቸው ብለዋል፡፡
42ቱ አቤቱታዎች ደግሞ በተቋሙ ተቀባይነት አግኘተው ለምርመራ የተመሩ እንደሆነም ተነስቷል፡፡

ተቋሙ ከተቀበላቸው 42 መዛግበት የመሬት ይዞታ ፣ የጡረታ እና የካሳ ክፍያ ከፍተኛውን ቁጥር እንደሚሸፍን ነግረውናል፡፡

ሰባት የሚሆኑ ተቋማት የተጣለባቸውን ውሳኔ ባለመቀበል የተቀመጡ አሉ የሚሉት አቶ ጸሃዬ ፤ ጉዳያቸውም ወደ ክስ ሄዶ በሂደት ላይ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ለአለም አሰፋ

ግንቦት 5 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *