ከ400 በላይ የሚሆኑና አይ ኤስ ለተባለ ታጣቂ ቡድን ለመዋጋት ወደ መካከለኛው ምስራቅ ተጉዘው የነበሩ ታጣቂዎች ወደ እንግሊዝ ተመልሰው መምጣታቸው ተገልጿል፡፡
በዚህም የእንግሊዝ የፓርላማ አባላት እነዚህ ዜጎች በመካከለኛው ምስራቅ ለፈጸሟዋቸው ወንጀሎች እንግሊዝ ሲገቡ ፍርድ ቤት መቅረብ አለባቸው ሲሉ ጠይቀዋል፡፡
የፓርላማ አባላቱ እነዚህ ግለሰቦች እስካሁን ምንም አይነት ክስ እንዳልተመሰረተባቸው ለሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ገልጸዋል፡፡
ስለዚህም የእንግሊዝ መንግስት እነዚህን በመካከለኛው ምስራቅ በትግል የቆዩ ታጣቂዎችን ለፍርድ ለማቅረብ አንቅስቃሴዎችን መጀመር እንዳለበት ጠይቀዋል፡፡
ማንኛውም ቡድንም ሆነ ግለሰብ በዘር ማጥፋት ወይም በጦር ወንጀል ከተጠረጠረ ምርመራ እንዲደረግበት የሚያስገድድ ህግ በሃገሪቱ መኖሩን በማሳሰብ ተግባራዊ እንዲሆን የፓርላማ አባላቱ አሳስበዋል ሲል የዘገበዉ ዘፔፐር ነው፡፡
ገነነ ብርሃኑ
ግንቦት 5 ቀን 2017 ዓ.ም
