ከ5 መቶ በላይ በማይናማር የሚገኙ ስደተኞች በአንድ ሳምንት ጊዜ ዉስጥ ወደ ኢትዮጵያ ይመለሳሉ ተብሏል፡፡
ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት የወላጆች ኮሚቴ አባል አቶ አስጨናቂ በቀለ፤ ትኬታቸው አክቲቭ የሆነ፣ ፓስፖርት ያላቸው፣ ፓስፖርት ያላቸው ሆኖም አመት ያለፈውን ጭምር የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሊያመጣቸው በተጠየቀው መሠረት እየተሰራ እንደሆነ ተናግረዋል።
ወደ አገር ከተመለሱት መካከል ትኬታቸው ጊዜው ስላለፈ 1መቶ5ዐ ዶላር የሚቀጡ ነበሩ ያሉት አቶ አስጨናቂ፤በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል ለአየር መንገዱ በቀረበው የትብብር ጥያቄ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቅጣቱን አንስቶላቸው መምጣታቸዉን ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በየቀኑ 80 ልጆችን ለማመላለስ ፕሮግራም መያዙንም አንስተዋል፡፡
ፕሮግራሙ የተቀመጠው ህንድ ባለው ኤምባሲ በኩል ኢትዮጵያን ወክለው ታይላንድ ካሉ ሰዎች ጋር በመነጋገር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባደረገው ጥረት እንደሆነ ገልጸዋል።
ሊዲያ ደሳለኝ
ግንቦት 5 ቀን 2017 ዓ.ም
