በአይቮሪኮስት የተቃዋሚው ፓርቲ መሪ ስልጣናቸውን በፍቃዳቸው መልቀቃቸውን አስታወቁ፡፡

የተቃዋሚው ፓርቲ መሪው ቲዲጃኔ ቲያም ከፓርቲያቸው ሊቀመንበርነት መልቀቃቸውን ካሳወቁ በኋላ፤ በፕሬዝዳንትነት አይቮሪኮስትን ለመምራት የሚደርጉትን የምርጫ ውድድር በግላቸው እንደሚቀጥሉበት ገልጸዋል፡፡

የፓርቲያቸው ፍላጎት ላይ በመንተራስ የፓርቲ መሪነት ስልጣናቸውን እንደለቀቁ የገለጹት ቲዲጃኔ ቲያም፤ ምርጫውን ለማሸነፍ ትግላቸውን እንደሚቀጥሉበት አስታዉቀዋል፡፡

የፕሬዝዳንትነት እጩዎች ጥምር ዜግነት እንዲኖራቸዉ በማይፈቅደው ህግ መሰረት ፤የተቃዋሚ ፓርቲው መሪ ቲዲጃኔ ቲያም የፈረንሳይ ፓስፖርት ስላላቸው ውድድራቸው እክል ሊገጥመው እንደሚችል ተገልጿል፡፡

እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር ከ 2011 ጀምሮ በስልጣን ላይ የሚገኙት የ 83 አመቱ ፕሬዝዳንት አላሳን አውታራ፤አሁንም በድጋሜ ለመወዳደር ፍላጎት እንዳላቸዉ ባይገልጹም ነገር ግን ሃገሬን ለማገልገል ሁሌም ጉጉት አለኝ ብለዋል ሲል አልጀዚራ አስነብቧል፡፡

ገነነ ብርሃኑ

ግንቦት 5 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *