በተለያዩ በሽታዎች ምክንያት 30 በመቶ የሚሆነው የቡና ምርት ለጉዳት እንደሚዳረግ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ባለሙያ የሆኑት አቶ ኢብሳ ኑሩ ገልፀዋል።
በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በግብርና ዘርፍ ባለሙያ የሆኑት አቶ ኢብሳ ኑሩ ከኢትዮ ኤፍም ጋር በነበራቸው ቆይታ ፤ቡናን ወቅቱን ጠብቀው ከሚከሰቱበት በሽታዎችና ተባዮች ለመከላከል አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ከፍተኛ ጥቅም እንዳለው ተናግረዋል።
አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ በተጨማሪም ፀረ-ተባይ እና ሌሎች ጎጂ ኬሚካሎች አጠቃቀምን ለመመጠንና ትክክለኛ የእርሻ ዘዴዎችን ለማዘጋጀት ጥቅም ላይ ይውላል ሲሉም አቶ ኢብሳ ኑር ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ በቡና ምርት ከአለም አምስተኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝና ኢትዮጵያ ወደ ዉጭ ከምትልካቸዉ ሌሎች ምርቶች መካከል ቡና 34 በመቶ ድርሻ እንደሚይዝ አስረድተውናል።
ይሁንና በቡና ግንድና ቅጠሎች ላይ በየወቅቱ በሚከሰቱ ልዩልዩ በሽታዎች ምክኒያት 30 በመቶ ምርት ለጉዳት ይዳረጋል ሲሉም ባለሙያዉ ጠቁመዋል፡፡
አሁን ላይ የቡና በሽታን ቀድሞ መለየት እና ማወቅ የሚያስችል የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ስርዓት ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
ልኡል ወልዴ
ግንቦት 7 ቀን 2017 ዓ.ም
