ባርሴሎና የ2024/25 የውድድር አመትየላሊጋው ሻምፒዮን ሆነ።

የስፔን ላሊጋን በሰማንያ አምስት ነጥቦች እየመራ የሚገኘው ባርሴሎና የላሊጋው 2024/25 የውድድር አመት አሸናፊ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

ባርሴሎና ከእስፓኞል ጋር ያደረገውን ጨዋታ 2ለ0 ማሸነፉን ተከትሎ ከወዲሁ ሁለት ጨዋታዎች እየቀሩ የሊጉ አሸናፊ መሆናቸውን ሊያረጋግጡ ችለዋል።

ባርሴሎናን አሸናፊ ያደረጉ ግቦች ላሚን ያማል እና ሎፔዝ አስቆጥረዋል።

ባርሴሎና ሀያ ስምንተኛ የስፔን ላሊጋ ዋንጫውን ማሸነፍ ችሏል።

ባርሴሎና በዚህ አመት የላሊጋ ፣ ኮፓ ዴላሬ እና ሱፐር ኮፓ ዋንጫዎችን በማሸነፍ የሀገር ውስጥ ሶስትዮሽ ዋንጫ አሳክተዋል።

ጋዲሳ መገርሳ

ግንቦት 8 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *