የቻይና ዜጎች ‘አደገኛ በሽታ አምጭ ተህዋሲያን’ ወደ አሜሪካ አስገብተዋል በሚል ተከሰሱ

ሁለት የቻይና ዜጎች የዩናይትድ ስቴትስ ባለስልጣናት ‘አደገኛ የስነ ሕይወት ተህዋሲያን’ ያሉትን ፈንገስ ወደ አሜሪካ በማስገባት ክስ ተመሰረተባቸው።

ያንኩንግ ጂያን እና ዙያንግ ሊዊ የተባሉ ሴት እና ወንድ ቻይናዊያን በማሴር፣ ሕገ ወጥ እቃዎችን በማስገባት፣ ሐሰተኛ ሰነድ በማቅረብ እንዲሁም ቪዛ በማጭበርበር መክሰሱን የሚቺገን ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ቢሮ አስታውቋል።

የ34 ዓመቱ ዙያንግ ሊዊ ፈንገሱን በዲትሮይት አየር ማረፊያ በማስገባት የ33 ዓመት ፍቅረኛው በምትሰራበት በሚችገን ዩኒቨርስቲ ቤተ ሙከራ ለማጥናት ሙከራ ማድረጉን የክስ ዝርዝሩ ያስረዳል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።

‘ፉሳሪየም ጋራሚነረም’ የተባለው ፈንገስ የስንዴ፣ ባቄላ፣ በቆሎ እና ሩዝ ሰብሎችን ሙሉ ለሙሉ የሚያጠፋ በሽታ የሚያስከትል ሲሆን ምግብ ላይ ሲገኝ ደግሞ የጉበት ጉዳት ያስከትላል።

ፈንገሱ በሳይንስ ጽሑፎች “እምቅ የግብርና የሽብር መሳሪያ” የሚል ስያሜ እንዳለው ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ገልጿል።

ቢቢሲ ለሚቺገን ዩኒቨርስቲ እና በዋሽንግተን ለቻይና ኤምባሲ አስተያየት እንዲሰጡ ጠይቋል።

ክሱ የቻይና እና አሜሪካ ግንኙነት በሻከረበት እና ከቀናት በፊት ፕሬዝዳንት ትራምፕ የቻይና ተማሪዎችን ቪዛ እንደሚነጥቁ በተናገሩበት ወቅት የመጣ ነው።

በሳምንቱ መጀመሪያ በሚቺጋን ዩኒቨርስቲ የሚማር ቻይናዊ በ2024ቱ ምርጫ በሕገ ወጥ መንገድ በመምረጥ ክስ ቀርቦበታል።

ግንቦት 27 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *