የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እንደገለጸዉ፤ወደ ጋዛ የደረሱት የእርዳታ መኪኖች ከ80 በመቶ በታች ናቸዉ፡፡
የተመድ ቃል አቀባይ ‹‹የመጣው ዕርዳታ አሁንም መሬት ላይ ያለውን ግዙፍ ፍላጎት አያሟላም›› ብለዋል፡፡
የተባበሩት መንግስታት እንዳስጠነቀቀው፤ በአከባቢዉ አሁንም የቦምብ ድብደባ እና መፈናቀል ተባብሶ በቀጠለበት ሁኔታ ወደ ጋዛ የሚደርሰዉ ድጋፍ በእጅጉ ያነሰ ነዉ በሚል ነዉ፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱጃሪች የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤትን በመጥቀስ፤ ከግንቦት 17 ጀምሮ ለሁለተኛ እና ለመጨረሻ ጊዜ የእስራኤልን ፍቃድ ለማግኘት ከቀረቡት የድጋፍ አቅርቦቶች ውስጥ ግማሹ ብቻ ወደ ፍልስጤም ማለፋቸዉን ገልጸዋል፡፡
በስፍራዉ ያሉ የሰብአዊ እርዳታ ሰጭዎች፤ባለፈው ወር በከፊል የተከፈተዉን የእርዳታ ማሸጋገሪያ በጥሩ ሁኔታ እየተጠቀሙበት ነዉ ያሉት ቃል አቀባዩ፤ በስፍራዉ የደረሰዉ እርዳታ ግን ብልጭልጭ ነው፤በመሬት ላይ ያለውን ግዙፍ ፍላጎቶችም አያሟላም ብለዋል፡፡
በአጠቃላይ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና አጋሮቻችን ከ1ሺህ2መቶ በላይ የጭነት መኪናዎችን ፍቃድ እንዲያገኙ ለእስራኤል አቅርበናል ያሉት ቃል አቀባዩ፤ይህ ሂደት ብዙውን ጊዜ ግልጽ የሆነ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
ከ80 በመቶ ያነሱት ተቀባይነት አግኝተው ከእስራኤል መጋዘኖች ተልከዋል ይህም ከ9መቶ40 በላይ የጭነት መኪኖች ናቸዉ፤ ከብዙ ቅኝት በኋላ ግን 6መቶ20 የሚሆኑት ብቻ ወደ ፍልስጤም ደርሰዋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የተባበሩት መንግስታት በሂደቱ ምንም አይነት ተሰሚነት እንደሌለው ገልፀው፤የእስራኤል ባለስልጣናት ማቋረጫ ላይ ተቆጣጣሪዎችን እንድናሰማራ አልፈቀዱልንም ስለሆነም ወደ 3መቶ70 የሚጠጉ የጭነት መኪናዎች ብቻ ድጋፉን አድርሰዋል ብለዋል፡፡
ሕይወት አድን የሆኑ ሰብዓዊ እንቅስቃሴዎችን ለማስተባበር ከ13ቱ ሙከራዎች መካከል 10 የሚሆኑት በእስራኤል ውድቅ መደረጋቸዉን ገልጸዉ፤ ውኃ ወደ ሰሜን ጋዛ ማጓጓዝ ወይም የነዳጅ ክምችቶችን ወደሚፈለጉበት ቦታ ማዛወርን ጨምሮ ብዙ የነፍስ አድን ድጋፎች ወደ ጋዛ እንዳይገቡ ሆኗል ሲሉ ገልጸዋል፡፡
በረሃብ፣ መፈናቀል እና በኢኮኖሚ ውዥንብር ምክንያት የህፃናት ጉልበት ብዝበዛ፣ ያለዕድሜ ጋብቻ እና የቤተሰብ መለያየት ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቷል ሲሉም አስጠንቅቀዋል፡፡
እስከዳር ግርማ
ግንት 27 ቀን 2017 ዓ.ም
