ፖርቹጋል ጀርመንን  2ለ1 በማሸነፍ  ለኔሽንስ  ሊግ  ፍፃሜ አልፋለች !

በኔሽንስ ሊግ ግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ፖርቹጋል ጀርመንን  2ለ1 በማሸነፍ ለፍፃሜ ማለፍ ችለዋል።

ለፖርቹጋል  ግቦቹን ክርስቲያኖ ሮናልዶ እና ኮንሴሳኦ ሲያስቆጥሩ ለጀርመን ፍሎሪያን ቨርትዝ ከመረብ አሳርፏል።

ፖርቹጋል በፍፃሜው የስፔን እና ፈረንሳይን አሸናፊ የፊታችን እሁድ የምትገጥም ይሆናል።

ፖርቹጋል ጀርመንን ከ25 አመታት  በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ማሸነፍ ችላለች።

የፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ክርስቲያኖ ሮናልዶ የጎል ብዛቱን ወደ 137 ከፍ ማድረግ ችሏል።

ክርስቲያኖ ሮናልዶ  ያስቆጠራቸውን አጠቃላይ ግቦች 937 ማድረስ ችሏል።

ክርስቲያኖ ሮናልዶ  ያስቆጠራቸውን የጨዋታ ማሸነፊያ ግቦች 296 አድርሷል።

ዛሬ  ምሸት 4:00 ላይ  ስፔን እና ፈረንሳይ ጨዋታቾውን ይደረጋሉ።

ጋዲሳ መገረሳ

ግንቦት 28 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *