ክልከላ የተደረገባቸው ሀገራት አፍጋኒስታን፣ ምያንማር፣ ቻድ፣ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ኢኳቶሪያል ጊኒ፣ ኤርትራ፣ ሄይቲ፣ ኢራን፣ ሊቢያ፣ ሶማሊያ፣ ሱዳን እና የመን ናቸው።
አዋጁ ከቀጣዩ ሰኔ 9 ጀምሩ ተግባራዊ ይሆናል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች እገዳውን ተችተውታል፣ አምነስቲ ኢንተርናሽናል እገዳውን “አድሎአዊ፣ ዘረኛ እና ጨካኝ” ሲል ገልፆታል።
ድርጅቶ በማህበራዊ ድረ-ገጽ X ላይ “ይህ እገዳ የተሳሳተ መረጃን እና ጥላቻን ብቻ ያሰራጫል” በማለት ገልጹታል።
የቬንዙዌላ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ዲዮስዳዶ ካቤሎ “በዩናይትድ ስቴትስ መገኘት ለቬንዙዌላውያን ብቻ ሳይሆን ለማንም ትልቅ አደጋ ነው” ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
ግንቦት 28 ቀን 2017 ዓ.ም
