ጽዱ ኢትዮጵያን ለመፍጠር 2ኛው የአካባቢ ብክለትን መከላከል ሀገራዊ ንቅናቄ በዛሬዉ ዕለት ተጀመረ።

በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ52ኛ ጊዜ በሀገራችን ለ32ኛ ጊዜ እየተከበረ ከሚገኘው የአለም የአካባቢ ቀን ጎን ለጎን መርሃግብሩ ተጀምሯል።

የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች የዜጎች ጤንነት እንዲጠበቅ፣ማህበራዊ ኑሯቸው እንዲሻሻል እና ጤናቸው እንዲጠበቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታሉ ተብሏል።

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ አደም ፋራህ 2ኛውን የአካባቢ ብክለት መከላከል ሀገራዊ ንቅናቄ በይፋ አስጀምረዋል።

አቶ አደም ፋራህ በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት÷ የአካባቢ ጥበቃ የቅንጦት ጉዳይ ሳይሆን የብልጽግናችን መሰረት ነው ብለዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በበኩላቸው፤ አለማችን የአየር ንብረት ለውጥ እያስተናገደች መሆኗን አንስተው፤ ሀገራችን በዚህ ላይ ያላት አስተዋጽኦ ጥቂት ቢሆንም በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በቢልዮኖች የሚቆጠሩ ችግኞችን ተተክለዋል ብለዋል።

በዚህም በአዲስ አበባ ከተማ ከነበረው የ2 ነጥብ 8 የደን ሽፋን ወደ 20 በመቶ ማሳደግ መቻሉን ገልጸዋል።

በመርሐ ግብር የክልል ርእሳነ መስተዳድሮችን ጨምሮ የፌዴራልና ክልሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ተገኝተዋል።

ሊዲያ ደሳለኝ

ግንቦት 28 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *