በአዲስ አበባ በቀን ከሚሰበሰበው ቆሻሻ 7በመቶ የሚሆነው ለማዳበሪያነት እየዋለ ነው ተባለ።

በአዲስ አበባ በቀን ከሚሰበሰበው ከ2ሺህ500 እስከ 3ሺህ ቶን ደረቅ ቆሻሻ ውስጥ ከ7 በመቶ በላይ ለማዳበሪያነት እየዋለ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ የፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ አስታውቋል።

ባለፉት 5 ዓመታት 94 በመቶ የሚሆነውን ቆሻሻ ወደ ሀብት መለወጥ ተችሏል ሲሉም የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር እሸቱ ለማ ተናግረዋል ።

የተሰበሰበ ደረቅ ቆሻሻን ወደ ሀብት ለመቀየር በሚሰራው ስራ ከ4አመት በፊት 2.5 በመቶ ብቻ መሆኑን የሚያስታውሱት ዋና ዳይሬክተሩ አሁን ላይ ግን 12.5በመቶ የሚሆነውን የደረቅ ቆሻሻ ወደ ሀብት መቀየር ተችሏል ብለዋል፡፡
በቀን ከሚመረተው የደረቅ ቆሻሻ መጠን አንፃር ግን አሁንም አጥጋቢ አለመሆኑን አንስተዋል።

ችግሩን ለመቅረፍ ለህብረተሰቡ ግንዛቤ የሚሰጡ ከ2ሺበላይ የግንዛቤ ሰጪ ባለሙያዎች ቢኖሩም በቂ አለመሆኑንም ገልፀዋል።
በሚባለው ልክ ውብ፣ፅዱ እና ለኑሮ ተስማሚ ከተማን ለመፍጠር ህብረተሰቡ ባለቤት መሆን አለበት ሲሉ ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

ሐመረ ፍሬው

ግንቦት 28 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *