ነገ ግንቦት 29 ቀን 2017 ዓ/ም የሚከበረውን 1446ኛው የኢድ አል አድሀ (አረፋ) በዓል ምክንያት በማድረግ መድፍ እንደሚተኮስ ኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ ፡፡
በኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ ሚኒስቴር የስነ ልቦና ግንባታ ዋና ዳይሬክቶሬት ለአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ በላከው ደብዳቤ 1446ኛውን የኢድ አል አድሀ (አረፋ) በዓል ምክንያት በማድረግ ነገ ግንቦት 29 ቀን 2017 ዓ/ም ከንጋቱ 12፡00 ሰዓት ላይ 9 (ዘጠኝ) ጊዜ መድፍ እንደሚተኮስ ገልጿል፡፡
በመሆኑም ህብረተሰቡ ተገቢው መረጃ እንዲኖረው ሲል የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል፡፡
ግንቦት 28 ቀን 2017 ዓ.ም
