አፍሪካ በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ ለማግኘት ጥረቷን ቀጥላለች

የአፍሪካ ህብረት አስር የሚኒስትሮች ኮሚቴ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ቢያንስ 2 ቋሚ መቀመጫዎች እና 5 ተለዋጭ ቦታዎችን ለመጠየቅ በዛምቢያ ስብሰባ እየተካሄደ መሆኑ ተሰምቷል፡፡

በዛምቢያ በተካሄደው 13ኛው የአፍሪካ ህብረት የአስር ኮሚቴ የሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት አባል እንድትሆን አፍሪካ የምታደርገው ጥረት ቀጥሏል ተብሏል፡፡

በዛምቢያ ዋና ከተማዋ ሉሳካ የተካሄደው ስብሰባ በአፍሪካ የጋራ አቋም ላይ ያተኮረ ሲሆን ይህም በተባበሩት መንግስታት ምክርቤት ውስጥ ቢያንስ ሁለት ቋሚ እና አምስት ተዘዋዋሪ ቦታዎችን ለአህጉሪቱ ለማስጠበቅ ያለመ እንደሆነ ተገልጹል፡፡

የዛምቢያው ፕሬዝዳንት ሃካይንዴ ሂቺሌማ በመክፈቻ ንግግራቸው እንደተናገሩት አህጉሪቱ በምክር ቤቱ ውስጥ ያለው ውሱን ውክልና የአፍሪካ ህብረት ግጭቶችን ለመፍታት እና ሰላምን ለማስጠበቅ ያለውን ውጤታማነት በእጅጉ ገድቦታል ብለዋል፡፡

“ይህ በተለይ በአህጉሪቱ እየተባባሱ ከመጡት ግጭቶች እና በፍጥነት እየተለዋወጠ ካለው የአለም ጂኦፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ገጽታ አንፃር አፍሪካ በጸጥታው ምክር ቤት አለመወከሉዋ ትልቅ ክፍተት መፍጠራቸውን ተናግረዋል፡፡

ስለዚህም የአፍሪካ ሀገራት አንድነታቸውን እና ከሌሎች አህጉር ሃገራት ጋር በተለይም አምስቱ የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ አባላት ጋር መተሳሰር አለባቸው ሲሉ ተደምጧል፡፤

የዛምቢያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሙላምቦ ሀይምቤ አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ውስጥ ቋሚ ውክልና የሌላት ብቸኛዋ አህጉር ናት ሲሉ በቁጭት ተናግረዋል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ፕሬዝዳንት ፊሊሞን ያንግ እንዳሉት አፍሪካ በምክር ቤቱ ውስጥ ቋሚ ውክልና ለማግኘት የምትጠቀምበትን ሞዴል እንድታቀርብ ተጠይቃለች።

የጽህፈት ቤታቸው ዳይሬክተር ኢቮር ፉንግ በሰጡት አስተያየት “ይህ ሞዴል ነው አፍሪካ በምክር ቤቱ ውስጥ ቋሚ ውክልና ለማግኘት የሚረዳት ብለዋል ሲል አናዱሉ ዘግቧል፡፡

ገነነ ብርሃኑ

ግንቦት 28 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *