በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ 11 ወራት ከውጭ ንግድ 7 .2 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር መገኘቱ ተገለፀ

እየተጠናቀቀ ባለው የበጀት ዓመት የመጀመሪያ 11 ወራት ኢትዮጲያ 7.2 ቢሊዮን ዶላር ማግኘቷን የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ አስታወቁ፡፡

ሚኒስትሩ ይሄን ያስታወቁት የፌደራል መንግስት የ2018 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀት ውይይት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እየተደረገበት ባለበት ወቅት ነው፡፡

ከባለፈው አመት ተመሳሳይ በጀት አመት ከተገኘው የ3. 3 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ጋር ሲነፀፃር የ118.2 በመቶ እድገት እንዳሳየ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

በኢትዮጲያ ከውጭ ንግድ ገቢ የተገኘ እጅግ ከፍተኛ ውጤት መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

ለዚህ ውጤት መገኘት የውጭ ምንዛሬ ማሻሻያው ጉልህ ሚና መጫወቱን የገን ዘብ ሚኒስትሩ አያይዘው አንስተዋል፡፡

አቤል እስጢፋኖስ

ሰኔ 3 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *