ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ከአሜሪካ ጋር ያደረገችው የማዕድን ስምምነት በሃገሪቱ ላይ ዘላቂ ሰላም ላያመጣ ይችላል ተብሏል

ኮንጎ ባለፉት አመታት ከገጠሟት አስከፊ ቀውሶች የእርስበርስ ጦርነት አንዱ ነው፡፡

የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ መንግስት ከኤም 23 ከተባለ አማፂ ቡድን ጋር በሃገሪቱ ምስራቃዊ ክፍል የለየለት ጦርነት ገጥሟል ፡፡

በእርስበርስ ጦርነቱ በዚህ አመት ብቻ ከ 7,000 በላይ ሰዎች ህይወት ሲቀጥፍ ከ7 ነጥብ 8 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን አፈናቅሏል፡፡

በመጋቢት ወር የኮንጎው ፕሬዝዳንት ፌሊክስ ከአሜሪካ ጋር ወሳኝ በሆኑ የማዕድን አቅርቦት ላይ በጋራ ለመስራት የተስማሙ ሲሆን በከፋ የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ በምትገኘው ኮንጎ የስምምነቱ ተግባራዊነት ላይ አጠራጣሪ ሆኗል፡፡

በርካታ ተንታኞች እንዳሉት ማንኛውም የማዕድን ስምምነት መጀመሪያ በሃገሪቱ የሚስተዋለውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም ፖለቲካዊ ችግሮች ካልተፈቱ የትም አያደርስም፡፡

እ.ኤ.አ. ከታህሳስ 2024 ጀምሮ የኤም 23 ተዋጊዎች የጎማ እና የቡካቩን – የሰሜን እና የደቡብ ኪቩ ዋና ከተማዎችን የጠቆጣጠሩ ሲሆን መንግስትና ታጣቂዎቹ በሃገሪቱ የማዕድን መገኛ አካባቢ በሚካሄደው ጦርነት ከፍተኛ ውጥረት መንገሱን የዘገበው አናዱሉ ነው፡፡

ገነነ ብርሃኑ

ሰኔ 5 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *