ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር )ህገወጥ የኮቴ ክፍያዎችን ለማስቀረት ክፍያ የሌለበት ይልቁንም ፍተሻ የተጠናከረበት የኬላ ቁጥጥር ስርዓት ይዘረጋል ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት ከመላው ሀገሪቱ ከተውጣጡ የንግዱ ማህበረሰብ ተወካዮች ጋር ባደረጉት ውይይት ከተሳታፊዎች ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ነው፡፡
በመድረኩ ህገወጥ የንግድ ስርዓቶች፣ የንብረት ታክስ፣ ሰላምና ደህንነት እንዲሁም የሙስና ጉዳዮች ከንግዱ ማህበረሰብ በኩል እንደ ችግር ተነስተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር ) በሰጡት ምላሽና ማብራሪያ፤ እየተነሱ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት በጋራ መስራት ይገባል ብለዋል።
ዲጂታል አገልግሎትን ማጠናከር የሌብነት በር የሚዘጋ በመሆኑ በቀጣይ በትኩረት እንደሚሰራበትም ተናግረዋል።
ሌብነትን በተመለከተ በመረጃ የተደገፈ ጥቆማ የሚቀርብ ከሆነ የትኛውም አመራር ተጠያቂ ይሆናል ሲሉም ተናግረዋል ።
ህገወጥ የኮቴ ክፍያዎችን ለማስቀረትም ክፍያ የሌለበት ይልቁንም ፍተሻ የተጠናከረበት የኬላ ቁጥጥር ስርዓት እንዘረጋለን ሲሉ ተናግረዋል።
ልኡል ወልዴ
ሰኔ 5 ቀን 2017 ዓ.ም
