የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከዲሲ ዩናይትድ ጋር የወዳጅነት ጨዋታ ይደረጋል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከዲሲ ዩናይትድ ጋር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወደ አሜሪካ አምርቶ የወዳጅነት ጨዋታ ለማድረግ  ስምምነት  አደረገ።

አቶ ባሕሩ ጥላሁን ከሁለት ዓመታት በፊት የተከናወነውን የአሜሪካ ጉዞ አውስተው በቡድኑ የአሜሪካ ቆይታ ወቅት ከአቶ ኢዮብ ማሞ ጋር የተፈጠረው ግንኙነት ከፍ ብሎ ባለፈው ዓመት የሸገር ደርቢን ማከናወን መቻሉን፣ ሱራፌል ዳኛቸው ወደ ላውደን ዩናይትድ እንዲያመራ በር መክፈቱን ተናግረዋል። የሴቶች ብሔራዊ ቡድን አንበል የሆነችው ሎዛ አበራ የዲሲ ፓወርን እንድትቀላቀል ይህ ስምምነት እንዳገዛቸውም አብራርተዋል።

ዲሲ ዩናይትድ   በቀጣይ 3 ዓመታት ብሔራዊ ቡዱኑን በዲሲ ዩናይትድ ሙሉ ወጪ ተሸፍኖለት ወደ አሜሪካ የሚያቀና ሲሆን የወዳጅነት ጨዋታዎች በማድረግ ተጫዋዎቻችን በመልማዮች የመታየት እድል ያገኛሉ ብለዋል። “ዲሲ ዩናይትድ ሙሉ ወጪውን ከመሸፈኑ በተጨማሪ ቡድናችን ጨዋታ በማድረጉ 25ሺህ ዶላር ያገኛል፤ በተጨማሪም ጨዋታ ካሸነፈ 50 ሺህ ዶላር ክፍያ የሚያገኝ ይሆናል።

ጋዲሳ መገርሳ

ሰኔ 6 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *