ኢራን እስራኤል በፈጸመችው ጥቃት ስድስት የኒውክሌር ሳይንቲስቶች መሞታቸውን አስታወቀች።

የኢራን ታስኒም የዜና ወኪል እንደዘገበው በእስራኤል ጥቃት ስድስት የኢራን የኒውክሌር ሳይንቲስቶች መገደላቸውን ዘግቧል።

ኤጀንሲው በኤክስ ላይ ባወጣው ዘገባ በጥቃቱ ስድስት ሳይንቲስቶች – አብዱልሃሚድ ሚኑችህር፣ አህመድሬዛ ዞልፋጋሪ፣ ሰይድ አሚርሆሴይን ፋቂ፣ ሞትላቢዛዴህ፣ መሀመድ መህዲ ቴህራንቺ እና ፌሬይዶን አባሲ ተገድለዋል ብሏል።

ሆሴይን ሳላሚ በዚህ ጥቃት ከተገደሉት ከፍተኛ አመራሮች መካከል አንዱ ናቸው።

የአገሪቱ የአቶሚክ ኢነርጂ ድርጅት ኃላፊ የነበሩት የኒውክሌር ሳይንቲስቱ ፍሬይዱን አባሲ መገደላቸውን የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

ፍሬይዱን አባሲ ለኢራን የኒውክሌር ማበልጸግ የአንበሳውን ድርሻ እንደተጫወቱ ይነገርላቸዋል።

ሳይንቲስቱ ከዚህ ቀደም በአውሮፓውያኑ 2010 በቴህራን ጎዳና ላይ ከተቃጣባቸው የግድያ ሙከራ ተርፈው ነበር።

ሌላኛው በዚህ ጥቃት የተገደሉት የኒውክሌር ሳይንቲስት በቴህራን የሚገኘው የእስላሚክ አዛድ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት መህዲ ቴህራንቺ ናቸው።

ኢራን አሜሪካ የእስራኤልን ጥቃት ደግፋለች ስትል የከሰሰች ሲሆን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ በበኩላቸው አገራቸው እንዳልተሳተፈች ተናግረዋል ሲል አልጀዚራ ዘግቧል።

ሰኔ 6 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *