የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ “ከቃላት በላይ የሆነ ልብ ሰባሪ ከስተት” ሲሉ ገልጸውታል የትላንቱን የአውሮፕላን አደጋ

ከሕንድ ወደ ለንደን የሚጓዝ የሕንድ አውሮፕላን ለበረራ እንደተነሳ ብዙም ሳይቆይ ተከስክሶ የበረራ አስተናጋጆችን ጨምሮ 241 ሰዎች እንዲሁም በተከሰከሰበት ሥፍራ የነበሩ በርካታ ሰዎች ሕይወት አልፏል።

ከምዕራባዊ ሕንድ አህመዳባድ ከተማ የተነሳው ቦይንግ 787-8 ድሪምላይነር አውሮፕላን የሆስፒታል ሕንፃ እና የህክምና ተማሪዎች ማደሪያ በሚገኝበት መኖሪያ አካባቢ ላይ ነው የተከሰከሰው።

በዚህ አደጋ በአውሮፕላኑ 11ኤ የወንበር ቁጥር ላይ ተቀምጦ የነበረ የእንግሊዝ ዜግነት ያለው መንገደኛ ብቻ በአስገራሚ ሁኔታ በሕይወት ተርፏል። ግለሰቡ በኋላ ላይ ለቤተሰቡ ሲናገር “እንዴት እንደተረፍኩ አላውቅም” ብሏል።

የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ “ከቃላት በላይ የሆነ ልብ ሰባሪ ከስተት” ሲሉ የገለጹት አደጋ መንስኤ እስካሁን ግልጽ አይደለም።

በሕንድ ታሪክ በርካቶች በሞቱበት በዚህ የአውሮፕላን አደጋ የሞቱ ሰዎች ቁጥርም ሊጨምር እንደሚችል ባለሥልጣናት ገልጸዋል።

በአውሮፕላኑ 169 የሕንድ ፣ 53 የእንግሊዝ፣ ሰባት የፖርቹጋል፣ አንድ የካናዳ ዜጎች በአጠቃላይ 230 መንገደኞችንና 12 የበረራ ቡድን አባላትን አሳፍሮ ነበር።

የአካባቢው ፖሊስ ለቢቢሲ እንደገለጸው እስካሁን 204 አስክሬኖች የተገኙ ሲሆን እነዚህ ሟቾች ግን አውሮፕላኑ በወደቀበት የመኖሪያ አካባቢ የነበሩ ይሁኑ አውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩ አልታወቀም።

ሰኔ 6 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *