ሆሴን ሰላሚ በእስራኤል ጥቃት መሞታቸውን ተከትሎ ጄኔራል አህመድ ቫሂዲ የእስላማዊ አብዮት ዘብ አዛዥ ሆነው ተሹመዋል።
ሀቢቦላህ ሳያሪ የጠቅላይ አዛዥ ጊዜያዊ ኃላፊ ሆነዋል።
እስራኤል ሌሊቱን በኢራን የኒውክሌር ሥፍራዎች እና የጦር አዛዦቿ ላይ ያነጣጠረ ከፍተኛ ጥቃት መፈጸሟን የእስራኤል መከላከያ ኃይል አስታውቃ ነበር።
በዚህ ከባድ በተባለው ጥቃት የኢራን አብዮታዊ ዘብ ኃላፊ ሆሴይን ሳላሚ መገደላቸውን የኢራን መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
እስራኤል ኢላማ ያደረግኩት ወታደራዊ ይዞታዎችን ነው ብትልም፤ የኢራን መገናኛ ብዙኃን በበኩላቸው በቴህራን የመኖሪያ ቤቶች ጥቃት እንደተፈጸመባቸው እና ከተገደሉትም መካከል ሲቪሊያን ይገኙበታል ብለዋል ሲል ስፑትኒክ ዘግቧል።
ሰኔ 6 ቀን 2017 ዓ.ም
