ይህ ኢራን እስካሁን ካደረገችው የተቀናጀ ጥቃት ትልቁ ነው። በክልሉ ውስጥ የአየር መከላከያ ስርዓቶች ሙሉ በሙሉ ንቁ መሆናቸው ተነግሯል፡፡
በሌላ በኩል የአሜሪካ፣ የእስራኤል እና የእንግሊዝ ተዋጊ ጄቶች ሰው አልባ አውሮፕላኖቹን ለመጥለፍ ከሶሪያ እና ኢራቅ የጦር ሰፈር መንቀሳቀስ ጀምረዋል፡፡
ዮርዳኖስ የአየር ክልሏን ለእስራኤል ተዋጊ ጄቶች መክፈቷም ተሰምቷል፡፡
ሳውዲ አረቢያ ጦርነቱን ከእስራኤል ጎን በመሆን ተቀላቅላለች፡፡
የሳውዲ ተዋጊ ጄቶች በየመን ድንበር እየተዘዋወሩ ከአንሷሩላህ የሚወነጨፉ ትንኮሳዎችን ለመጥለፍ በዝግጅት ላይ ናቸው ተብሏል።
የብሪታንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴቪድ ላሚ እስራኤል በኢራን በአንድ ሌሊት ያደረሰችውን ጥቃት ‘አደገኛ ‘ ሲሉ ገልፀው ሁሉም ወገኖች ራሳቸውን እንዲቆጣጠሩ አሳስበዋል ሲል RT ዘግቧል ።
አሁን እየወጡ ያሉ ሪፖርቶች እንደሚያመለክቱት ከ800 በላይ የኢራን ፕሮጄክቶች—ክሩዝ ሚሳኤሎች፣ ባለስቲክ ሚሳኤሎች እና የአጥፍቶ ጠፊ ድሮኖችን ጨምሮ—ወደ እስራኤል ተተኩሰዋል።
ሰኔ 6 ቀን 2017 ዓ.ም
