የዓለም የደምና የአይን ብሌን ልገሳ ቀን በነገዉ ዕለት ይከበራል፡፡

የደምና ህብረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት በየዓመቱ ሰኔ 3 እና ሰኔ 7 አለም አቀፍ የአይን ብሌን ለጋሾች እና የደም ለጋሾችን ቀን ያከብራል።

ነገ የሚከበረዉ አለም አቀፍ የደም ለጋሾች ቀን ሰኔ ወርን ምክንያት በማድረግ ይከበራል።

በመሆኑም ወሩን በተለያዩ የንቅናቄና የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎችና በበጎ ፍቃድ የደም ማሰባሰብ ስራ ለማክበር እንቅስቃሴ እየተደረገ እንደሆነ በኢትዮጵያ ደምና ህብረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት የህዝብ ግንኙነት ኮሚንኬሽን ስራ አስፈጻሚ አቶ አለማየሁ ታረቀኝ ከጣቢያችን ጋር በነበራቸዉ ቆይታ ገልጸዋል፡፡

መጭዉ ጊዜ ክረምት በመሆኑ እና ትምህርት ቤቶችም ስለሚዘጉ የደም ዕጥረት እንዳይከሰት ህብረተሰቡን ለማንቃትና በመደበኝነት በየሶስት ወሩ ደም እንዲለገስና ለማህበረሰቡ ግንዛቤ ለመስጠት እንደሆነ አንስተዋል፡፡

በዕለቱም ለተባባሪ አካላት የዕውቅናና የምስጋና መርሀ ግብር እንዳለም ተናግረዋል።

ሊዲያ ደሳለኝ

ሰኔ 6 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *