የእስራኤል ጥቃት እና የኢራን አጸፋ አሁንም ቀጥሏል

እስራኤል በኢራን ላይ ጥቃት በመክፈት የጀመረችው ፍጥጫ አርብ ለቅዳሜ አጥቢያ ሌሊትም ቀጥሏል።

ኢራን ወደ እስራኤል ያሰወነጨፈችውን ባለስቲክ ሚሳኤል ተከትሎ የከተሞች የማስጠንቀቂያ ደወሎች እየተሰሙ መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል ።

በዚህ ጥቃት ቢያንስ ሁለት እስራኤላውያን ሲገደሉ በርካቶች መቁሰላቸው ሪፖርት ተደርጓል።

በሁለቱም አገራት ውስጥ የአየር ጥቃቶች እና ፍንታዳታዎች መከሰታቸው ተዘግቧል።

ኢራን የአጸፋ ሚሳዔሎችን ወደ እስራኤል በመተኮሷ በቴል አቪቭ እና ኢሩሳሌም ውስጥ የአየር ጥቃት ማስጠንቀቂያ ደወሎች እና ሲሰሙ ቴህራን ውስጥ ፍንዳታዎች ተሰምተዋል።

የኢራን የበላይ መሪ አያቶላህ ኻሜኒ እስራኤል በአገራቸው ላይ ለፈጸመችው ጥቃት “ከባድ አጻፋ” እንሚጠብቃት ዝተዋል።

ኢራን ወደ እስራኤል በተኮሰቻቸው ሚሳዔሎች ተጎድተዋል የተባሉ 40 ያህል ሰዎች ወደ ሆስፒታል መግባታቸው እና ከመካከላቸውም ሁለቱ በጽኑ መጎዳታቸው ተዘግቧል።

የኢራን አብዮታዊ ዘብ እንዳለው በእስራኤል ላይ ባለስቲክ ሚሳዔሎችን ሲተኩስ፣ የእስራኤል ጦር ሠራዊት ደግሞ ሚሳዔሎቹን ማክሸፉን አስታውቋል።

በተባበሩት መንግሥታት የኢራን መልዕክተኛ በእስራኤል ጥቃት ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦችን ጨምሮ 78 ሰዎች መገደላቸውን እና ከ320 በላይ የሚሆኑ ደግሞ መቁሰላቸውን አስታውቀዋል።

አሜሪካ እስራኤልን በመደገፍ ስትቆም፣ ቻይና እና ቱርክ የእስራኤልን ድርጊት በማውገዝ አቋማቸውን ገልጸዋል።

የተባበሩት መንግሥታት እና ሌሎች አገራት ደግሞ ኢራን እና እስራኤል ግጭቱን ከሚያባብሱ እርምጃዎች እንዲቆጠቡ ጥሪ አቅርበዋል።

ሰኔ 7 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *