ነገ በጅማ ከተማ ይጀመራል።
የ6ኛው መላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎችን በማሰመልክት የፓናል ውይይት ተከናውኖዋል።
6ኛው የመላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎች “ስፖርት ለህብር ኢትዮጵያ አርበኝነት” በሚል መሪ ቃል ከሰኔ 10-19/2017
በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በጅማ ከተማ ከነገ ጀምሮ የሚከናወንም ይሆናል።
ያንን አስመልክቶ የፓናል ውይይት በጅማ ዩኒቨርስቲ ቅጥር ግቢ አዳራሽ ላይ ተከናውኗል።
የሀገር ሽማግሌዎች እና የተለያዩ የሀይማኖት አባቶች መልካም ምኞታቸውን እንዲሁም ምርቃት በመስጠት ዝግጅቱ ተጀምሯል።
የባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ የሆኑት አቶ መክዩ መሀመድ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን ፤ የቀድሞ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ፤ እንዲሁም የባህል ስፖርቶች ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ህይወት አህመድ እንዲሁም ሌሎች እንግዶች ሀገኝተዋል።
የሀገር ሽማግሌዎች እና የተለያዩ የሀይማኖት አባቶች መልካም ምኞታቸውን እንዲሁም ምርቃት በመስጠት ዝግጅቱ ተጀምሯል።
የባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ የሆኑት አቶ መክዩ መሀመድ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
አቶ አህመድ መህመድ ፤ ዶ/ር ዋቅጅራ ሲማ እንዲሁም አቶ ፀጋዬ ማሞ ባጠቃላይ ስፖረትት ለብሄራዊነት ግንባታ እና ለማህበራዊ አብሮነት ያለው ፋይዳ ፤ ስለ ስፖርት ታሪካዊ አመጣጥ ፤ ስፖርት ለሰላም እና አንድነት የሚሰጠው እንዲሁም የሚኖረውን ፖለቲካዊ ፋይዳ በጥናታዊ ፆሁፍ መልክ አቅርበዋል።
በመጨረሻም ከከተማው የተወጣጡ የማህበረሰብ አካላት ለተሰነዘሩ ሀሳብ እና ጥያቄዎችን በማስተናገድ መድረኩ ተጠናቋል።
የነገ የመክፈቻው ዕልት ፕሮግራሞች
የማሰ ሰፖርት ንጋት 11:00-01:00
የመክፈቻ ፕሮግራም በጀማ ዩኒቨርሲቲ ሰታዲዮም 4:00-8:00
የምሳ ፕሮግራም 8:00-9:00
የገጠር ኮሪደር ልማት ጉብኝት 9:00-10:00
የጀማ ከተማ ኮሪደር ፣የገበታ ለሀገር ፕሮጀክት እና አባ ጅፋር ቤተ መንግሰት ጉብኝት 10:00-12:00
የእራት ግብዣ 12:00-01:00
ሰኔ 9 ቀን 2017 ዓ.ም
