የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በጋዛ የሚገኙ የእስራኤል ምርኮኞችን ለማስፈታት የሚደረጉ ንግግሮች ‹‹እንዲፋጠኑ›› ለተደራዳሪዎች መመሪያ ሰጥተዋል።
እስራኤል በቅርቡ በኢራን ላይ መጠነ ሰፊ ጥቃት ካደረሰች በኋላ፤ ሁኔታዉን ነገሮች የሚሻሻሉበት ዕድልን ይዞ የመጣ ነዉ ብለዋል፡፡
ከፍልስጤሙ ተቃዋሚ ቡድን ጋር በምርኮኞች ዙሪያ እየተደረገ ያለዉን ዉይይት በማንሳት፤ድርድሩን ለማፋጠን መመሪያ ሰጥቻለሁ፤ ሁለቱንም ተልእኮዎች ማለትም የሃማስን መጥፋት እና የታጋቾችን መለቀቅን መፈጸም የምንችልበት ዕድል እንዳለ ይሰማኛል ሲሉ ኔታንያሁ በቪዲዮ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
በጥቅምት 7 ሃማስ በእስራኤል ላይ ባደረሰዉ ጥቃት 2መቶ51 ሰዎች በምርኮ ተወስደዋል፡፡
ከነዚህ ውስጥ 52ቱ አሁንም በጋዛ ታስረዉ የሚገኙ ሲሆን፤ የእስራኤል ጦር እንደዘገበው 34ቱ ተገድለዋል ተብሎ ይታመናል።
ሃማስ በ2014ቱ ጦርነት ወቅት የተገደለውን የእስራኤል ወታደር አስክሬን ዛሬም ድረስ መያዙንም ከቴል አቪቭ የወጡ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡
እስከዳር ግርማ
ሰኔ 10 ቀን 2017 ዓ.ም
