የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከካናዳው አውሮፕላን አምራች ሁለት ሞዴሎችን አዘዘ

አየር መንገዱ የመጀመሪያዎቹን የደሃቪላንድ ካናዳ ዲኤችሲ-6 ትዊን ኦተር 300-ጂ ሞዴሎች ለመግዛት ትናንት ስምምነት ተፈራርሟል።

አውሮፕላኖቹ ውሃና መሬት ላይ ማረፍ እና መነሳት የሚችሉ ናቸው። ይህም በኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኙ ሩቅ እና የሐይቅ አካባቢዎች ተሳፋሪዎችን ለማጓጓዝ ያግዛል ተብሏል።

ለማረፍ እና ለመነሳት ትንሽ ደቂቃ የሚወስድባቸው እነዚህ አውሮፕላኖች ለአስቸጋሪ መልክዓ ምድሮችና ውስን መሠረተ ልማቶች ባሉባቸው ቦታዎች ከመድረሳቸው ባሻገር ለጭነት፣ ለአየር አምቡላንስ እና ለቻርተር አገልግሎት እንደሚውሉ ተነግሯል።

ሰኔ 11 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *