የእስራኤል መከላከያ ኃይል የእስራኤል ሰው አልባ አውሮፕላን በኢራን መመታቱን አረጋግጧል

“መሣሪያው በኢራን አየር ክልል ውስጥ ወድቋል፣ ምንም አይነት ጉዳት አልደረሰም ፤ መረጃ ይወጣል የሚል ፍራቻ የለም” ሲል የመከላከያው ቃል አቀባይ ተናግሯል።

ዛሬ ማለዳ የኢራን መገናኛ ብዙኃን አንድ የእስራኤል ኤፍ-35 ተዋጊ ጀት ከቴህራን አቅራቢያ ቫራሚን ላይ ተመትቶ ወድቋል ሲሉ ዘግበዋል።

የኢራን የአየር መከላከያ ኃይል በማዕከላዊው ኢስፋሃን ግዛት ውስጥ ጥቃት ለመፈጸም የተሰማራ ሄርሜስ የተባለ ዘመናዊ የእስራኤል ድሮን መትቶ መጣሉን የኢራን መንግሥት ቴሌቪዥን አስታወቋል።

የጣቢያው ዘጋቢ ድሮኑ ከወደቀበት ስፍራ ካለ ስብርባሪ ጎን ቆሞ ተመትቶ የወደቀው በአገሪቱ ሰዓት አቆጣጠር ዛሬ ንጋት 11 ሰዓት ላይ መሆኑን ገልጿል።

ዘጋቢው ጨምሮም ድሮኑ ተመትቶ የወደቀው የታጠቀውን መሳሪያ ከመተኮሱ በፊት መሆኑን እና የኢራን አየር መከላከያ ኃይልን ቀድሞ የመለየት እና ምላሽ የመስጠት ብቃትን ገልጿል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።

ሰኔ 11 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *