ጀርመን ለኢራን ለመደራደር ፈጽሞ አይረፍድም ስትል መልዕክት ልካለች።

የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የኢራን መሪዎች አገሪቱ የኒውክሌር ጦር መሳሪያ እንደማትፈልግ ተአማኒነት ያለው ማረጋገጫ እንድትሰጥ ጠይቀዋል፡፡

በኢራን እና በእስራኤል መካከል ወታደራዊ ግጭቱ ተባብሶ እንዳይቀጥል በድርድር መፍትሄ ለመፈለግ ፈቃደኛ መሆኗን እንዲያሳዩ ተማጽነዋል።

ሚኒስትሩ ከዮርዳኖስ አቻቸው ጋር በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ መፍትሄውን ለማደራደር ዝግጁ ነን፤ሆኖም ኢራን አስቸኳይ እርምጃ መውሰድ አለባት ብለዋል፡፡

አንድ ሰው በቅን ልቦና ወደ ድርድር ጠረጴዛው ለመምጣት ፍላጎት ካሳየ ለመደራደር ፈጽሞ አልረፈደም ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ኢራን ቀጣይ ዙር የኒውክሌር ድርድር ሊካሄድ ጥቂት ቀናት ሲቀረው የእስራኤልን ድንገተኛ ጥቃት ተከትሎ በአሜሪካ እና በምዕራባውያን አጋሮቿ ላይ ምንም አይነት እምነት እንደሌላት መናገሯን የዘገበዉ አልጀዚራ ነዉ።

ሊዲያ ደሳለኝ

ሰኔ 11 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *