አሜሪካ በኢራን ላይ የፈጸመቻቸውን ጥቃቶች ተከትሎ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ ዜጎችን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ማስጠንቀቂያ አውጥቷል።
ዓለም አቀፍ የደህንነት ማስጠንቀቂያ የወጣው በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል ነው።
“በአሜሪካ ዜጎች እና ብሄራዊ ጥቅሞችን የተጻረሬ የተቃውሞ ሰልፎች ሊደረጉ ይችላሉ። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስት በዓለም ዙሪያ ያሉ አሜሪካውያን ዜጎች የበለጠ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ይመክራል” ብሏል።
አሜሪካ ይህንን ማስጠንቀቂያ ያወጣችው በኢራን የኒውክሌር ይዞታዎች ላይ ከባድ የተባለ ጥቃት መፈጻሟ ተከትሎ ነው፡፡
ዶናልድ ትራምፕ አገራቸው በኢራን ላይ የፈጸመችውን ጥቃቶች “በሁሉም የኒውክሌር ይዞታዎች” ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰ፤ እንዲሁም “ማውደም የሚለው” የሚገልጸው ነው ብለዋል።
ትራምፕ ትሩዝ ሶሻል በተሰኘ ማህበራዊ ሚዲያቸው ላይ በጽሁፉ ላይ ያላካፈሉትን የሳተላይት ምስል በመጥቀስ “የሚታየው ነጭ መዋቅር በድንጋይ የተከበበ ነው፤ ከእሳቱም ተከልሏል” ብለዋል።
ሆኖም “ከፍተኛው አደጋ የደረሰው ከመሬት በታች ባለው ይዞታው ነው ብለዋል።
አክለውም “ማዕከሉን መትተነዋል” ሲሉ ገልጸዋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።
ሰኔ 16 ቀን 2017 ዓ.ም
