6ኛው መላው ኢትዮጵያ ጨዋታ ነገ ፍፃሜውን ያገኛል።

በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር አዘጋጅነት ከሰኔ 10፣ 2017ዓ.ም ጀምረሸ ሲካሄድ የቆየው 6ኛው መላው ኢትዮጵያ ጨዋታ ነገ ፍፃሜውን ያገኛል።

በዚህ ውድድር በርካታ ስፖርቶች ፍፃሜያቸውን አግኝተዋል።

የውኃ ዋና ስፖርት ሌላኛው ፍፃሜውን የገኘ ሲሆን አማራ   
በአጠቃላይ 22 ወርቅ 10 ብር እና 12 ነሐስ በድምር 44 ሜዳሊያ በማምጣት አሸናፊ ኾኗል።

አዲስ አበባ 15 ወርቅ እና ኦሮሚያ 8 ወርቅ በማምጣት ሁለተኛ እና ሦስተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።

የአማራ ክልል ኮከቦችንም ሲያስመርጥ በግል 8 የወርቅ፤ በቡድን 4 ተጨማሪ የወርቅ ሜዳልያዎችን ያሳካው ተምኪን ጌታቸው የውድድሩ ክስተት ኾኗል።

በእጅ ኳስ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ አዲስ አበባ እና ኦሮሚያ ከ1-3 ያለውን ደረጃ ይዘው ሲያጠናቅቁ በክብደት ማንሳት ስፖርት በወንዶች ኦሮሚያ፣ አማራና አዲስ አበባ በደረጃ አጠናቀዋል።

በሴቶች ቤንሻንጉል፣ ኦሮሚያና ደቡብ ኢትዮጵያ ከ1-3 ያለውን ደረጃ በመያዝ ወርቅ፣ ብርና ነሀስ ተሸላሚ ሆነዋል።

እግር ኳስ የፍፃሜ ውድድር በወንዶችም በሴቶችም  ኦሮሚያ ከ ደበቡ ኢትዮጵያ ሀሙስ ይጫወታሉ።

ጋዲሳ መገርሳ

ሰኔ 18 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *